AMHARIC NEWS

  • BBC AMHARIC
  • DW AMHARIC

በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን ደቡብ ሜጫ ወረዳ ሐምሌ 15/2016 ዓ.ም. ‘ከመንግሥት ጋር ስብሰባ ተቀምጠው ነበር’ የተባሉ የአካባቢው ነዋሪዎች በታጣቂዎች ማሰቃየት እና ግድያ ተፈጸሞባቸዋል። ለመሆኑ ለግለሰቦቹ እንግልት እንዲሁም ሞት ምክንያቱ ምንድን ነው? ተሳተፈውበታል የተባለውስ ስብሰባ በማን የተዘጋጀ ነበር? መረጃውስ ከየት መጣ? የቀሩትስ ሰዎች ዕጣ ፈንታ ምን ሆነ? ለሚሉት ጥያቄዎች ቢቢሲ ምላሽ አግኝቷል። [...]

መሰለች ከሰኞ ጀምሮ ለባሏ እና ለልጆቿ እያለቀሰች ከአደጋው ስፍራ አልተለየችም። አደጋው ከደረሰ አምስት ቀናት ያለፉ ቢሆንም ተስፋ አልቆረጠችም። ብቻዋን ላለመቅረት አንደኛው ልጇ ይገኛል ብላ በደበዘዘ ተስፋ እየጠበቀች ነው። [...]

በመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ አትሌቶች ሲን ወንዝን ተሻግረዋል። በወንዙ ዳርቻ እንዲሁም ወንዙን በሚያቋርጠው ድልድይ ላይ የተለያዩ ትርዒቶች ቀርበዋል። [...]

ወቅቱ የአውሮፓውያኑ 1996 ነበር። በአሜሪካዋ የአትላንታ ሴንተኒያል የኦሊምፒክ ስታዲየም ፍልስጤማዊው ማጅድ አቡ ማራሄል የፍልስጤምን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ አድርጎ እያውለበለበ ይዞ ገባ። ለመጀመሪያ ጊዜ ሰንደቅ ዓላማዋ ስትውለበለብ በርካቶች በደስታ አነቡ። [...]

ኡጋንዳዊው የመብት ተሟጋች እስር ቤት ውስጥ በፖሊስ ወሲባዊ ጥቃት እንደደረሰበት ተገለጸ። [...]

የኤርትራ መንግሥት የአቪየሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ ወደ አስመራ በረራ እንዳያደርግ ያገደበት ውሳኔ ላይ ለመነጋገር እና ለመመካከር ሙከራ እያደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ። አየር መንገዱ የተፈጠረው ችግር በሰላም ተፈትቶ ወደነበረበት እንደሚመለስ ተስፋ ያደርጋል። [...]

ለረጅም ዓመታት ከፍተኛ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሀገር ውስጥ መንገደኞች ማስተናገጃ ማእከል የተጓዦችን የፍላጎት እድገት መነሻ ተደርጎ የተሠራ የማዘመን ሥራ ነው ሲሉ የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አሥፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው ተናግረዋል። [...]

የአየር ካርጎ አገልገሎቱ ወደ ኢ-ኮሜርስ አገልግሎት ማደግ አለበት ያሉት አቶ መስፍን ጣሰው ዛሬ ግንባታው ተጠናቆ የተመረቀው የካርኮ መጋዘን ከተለመደው የሚለየው፤ ትናንሽ እቃዎች በጥቅል መጥተው ግን እዚህ ተበትነው ለደንበኞች የሚደርሱበት አሰራር የሚዘረጋ በመሆኑ ነው በማለት አየር መንገዱ ዘርፉን መቀላቀሉን አረጋግጠዋል። [...]

ከስምንት አስርተ አመታት በፊት አውሮፕላን ለመገጣጠም ጥረት ያደረገችው ኢትዮጵያ፤ በአፍሪቃ ስሙ የሚጠቀሰስ አየር መንገድ በመመስረትም ቀዳሚ ሀገር ነች።ለመሆኑ ሀገሪቱ በአሁኑ ወቅት በአቬሽን ቴክኖሎጂ ምን ደረጃ ላይ ትገኛለች? በዘርፉ ያሉ ችግሮች እና መፍትሄዎችስ? [...]

ለወጣቶች «ጠቃሚ ናቸው» ብሎ በሚያጋራቸው መረጃዎቹ በርካታ የቲክቶክ ተጠቃሚዎች መላኩ በላይን ያውቁታል። ከዚህም በተጨማሪ በትወና ስራ ተሳታፊ ነው። ቲክቶክ ላይ የሚለጥፋቸውን ቪዲዮዎች ከ 1,4 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ወደውለታል፣ ከ 108 ሺ በላይ የሚሆኑ ደግሞ ይከተሉታል። ለምን ይሆን? [...]

ዜና