AMHARIC NEWS

  • BBC AMHARIC
  • DW AMHARIC

እስካሁን ከ250 በላይ ሰዎች እንደሞቱበት በተረጋገጠው የጎፋ ዞን የመሬት መንሸራተት የተቀበሩ ሰዎችን ለማውጣት ፍለጋው አሁንም ቀጥሏል። በአደጋው የሞቱ ሰዎች ቁጥር እስከ 500 ሊደርስ እንደሚችል የአካባቢው ባለሥልጣናት ይናገራሉ። አካባቢው መሠረተ ልማት የሌለው እና ራቅ ያለ በመሆኑ የመቆፈሪያ መሳሪያዎችን ለማስገባት ባለመቻሉ ቁፋሮው በሰው እጅ እየተደረገ ነው። [...]

በፈረንሳይ ዛሬ፣ ሐምሌ 19/ 2016 ማለዳ በፈጣን ባቡር መስመሮች ላይ የእሳት ቃጠሎ ጥቃቶች መፈጸማቸውን ባለስልጣናቱ ተናገሩ። በዛሬው ዕለት ከሰዓታት በኋላ በሚከፈተው የፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር ቀደም ብሎ ይህ መፈጸሙ “በፈረንሳይ ላይ የተቃጣ ጥቃት” እና ወደ መክፈቻው የሚደረጉ ጉዞዎችን ለማስተጓጎል የተፈጸመ አሻጥር ነው ስትልም አውግዛለች። [...]

ኤርትራ በሰባ ሁለት ሰዓት ውስጥ ከግዛቷ እንዲወጡ ያዘዘቻቸውን ዲፕሎማቷን በሚመለከት ሱዳን ማብራሪያ መጠየቋ ተነገረ። መንግሥታዊው የሱዳን ዜና አገልግሎት ሱና እንደዘገበው የሱዳን መንግሥት በጎረቤት አገር በኤርትራ የነበሩት ጉዳይ ፈጻሚው (ቻርጅ ዲ አፌር) ስለተባረሩበት ምክንያት “ማብራሪያ” ጠይቆ ምላሽ እየተጠባበቀ ነው። [...]

በሰሜን ኢትዮጵያ በድርቅ፣ ሰብል ባለመሰብሰቡ እና ከጦርነቱ በኋላ በቀጠለ አለመረጋጋት ምክንያት ሰብዓዊ ቀውስ እየተባባሰ መምጣቱ ተነግሯል። የአካባቢው ባለሥልጣናት ከሁለት ሚሊዮን በላይ ሰዎች ለረሀብ እንደተጋለጡ ያስጠነቀቁ ሲሆን፣ ቢቢሲ ከሳተላይት ምሥሎች ባጣራው መረጃ መሠረት በትግራይ የከፋ ሰብዓዊ ቀውስ እየተከሰተ ነው። [...]

አንድ የአውስትራሊያ የሆኪ (የገና ጨዋታ ዓይነት ስፖርት) ተጫዋች በፓሪስ ኦሊምፒክ ለመወዳደር ሲል የጣቱን የተወሰነ ክፍል እንዲቆረጥ ማስደረጉ ተነገረ። [...]

የኤርትራ መንግሥት የአቪየሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ ወደ አስመራ በረራ እንዳያደርግ ያገደበት ውሳኔ ላይ ለመነጋገር እና ለመመካከር ሙከራ እያደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ። አየር መንገዱ የተፈጠረው ችግር በሰላም ተፈትቶ ወደነበረበት እንደሚመለስ ተስፋ ያደርጋል። [...]

ለረጅም ዓመታት ከፍተኛ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሀገር ውስጥ መንገደኞች ማስተናገጃ ማእከል የተጓዦችን የፍላጎት እድገት መነሻ ተደርጎ የተሠራ የማዘመን ሥራ ነው ሲሉ የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አሥፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው ተናግረዋል። [...]

የአየር ካርጎ አገልገሎቱ ወደ ኢ-ኮሜርስ አገልግሎት ማደግ አለበት ያሉት አቶ መስፍን ጣሰው ዛሬ ግንባታው ተጠናቆ የተመረቀው የካርኮ መጋዘን ከተለመደው የሚለየው፤ ትናንሽ እቃዎች በጥቅል መጥተው ግን እዚህ ተበትነው ለደንበኞች የሚደርሱበት አሰራር የሚዘረጋ በመሆኑ ነው በማለት አየር መንገዱ ዘርፉን መቀላቀሉን አረጋግጠዋል። [...]

ከስምንት አስርተ አመታት በፊት አውሮፕላን ለመገጣጠም ጥረት ያደረገችው ኢትዮጵያ፤ በአፍሪቃ ስሙ የሚጠቀሰስ አየር መንገድ በመመስረትም ቀዳሚ ሀገር ነች።ለመሆኑ ሀገሪቱ በአሁኑ ወቅት በአቬሽን ቴክኖሎጂ ምን ደረጃ ላይ ትገኛለች? በዘርፉ ያሉ ችግሮች እና መፍትሄዎችስ? [...]

ለወጣቶች «ጠቃሚ ናቸው» ብሎ በሚያጋራቸው መረጃዎቹ በርካታ የቲክቶክ ተጠቃሚዎች መላኩ በላይን ያውቁታል። ከዚህም በተጨማሪ በትወና ስራ ተሳታፊ ነው። ቲክቶክ ላይ የሚለጥፋቸውን ቪዲዮዎች ከ 1,4 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ወደውለታል፣ ከ 108 ሺ በላይ የሚሆኑ ደግሞ ይከተሉታል። ለምን ይሆን? [...]

ዜና