AMHARIC NEWS

  • BBC AMHARIC
  • DW AMHARIC

የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነትን ተከትሎ በአማራ ክልል ስር ሲተዳደሩ የቆዩት የራያ አካባቢዎች ያለ አስተዳዳሪ ወደ ሁለተኛ ሳምንታቸው እየተሻገሩ ነው። ከየካቲት ጀምሮ አልፎ አልፎ ሲከሰት የነበረው “በህወሓት ታጣቂዎች” እና “በአካባቢው ሚሊሺያዎች” መካከል ሲደረግ የነበረው የተኩስ ልውውጥ ከሚያዝያ 5/2016 ዓ.ም. ጀምሮ ከፍ ባለ ሁኔታ ተካሂዶ ከሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ወዲህ የነበረውን መዋቅር ቀይሮታል። [...]

አንዲት ኤርትራዊት ስደተኛ ፖላንድ እና ቤላሩስ ድንበር ላይ ብቻዋን ሆና ወልዳለች ከተባለ በኋላ ፖላንድ ስደተኛዋን ከድንበር አልመስኩም አለች። [...]

የአየርላንድ መንግሥት ከዩናይትድ ኪንግደም የሚመጡ ስደተኞችን ወደ ዩኬ መመለስ የሚያስችለውን ሕጋዊ ማዕቀፍ ማዘጋጀት ጀመረ። [...]

ሐማስ ያወጣው ቪዲዮ አንድ አሜሪካዊ እና አንድ እስራኤላዊ ታጋቾች በጋዛ በሕይወት እንደሚገኙ ማረጋገጫ ሆኗል ተባለ። [...]

በአሜሪካ ዴንቨር ግዛት የሚገኘው ዊትየር ካፌ፣ ከአንድ ስኒ ቡና ወይንም ኤስፕሬሶ ከፍ ያለ ነገር ለደንበኞቹ ማቅረብ ይፈልጋል። ካፌው ከአፍሪካ ከሚያስመጣቸውን ቡናዎች የሚያፈላው ኤስፕሬሶ ሀሳቦችን ለማንሸራሸር ቢረዱ ሲል ይመኛል። በካፌው የኢትዮጵያ፣ የሩዋንዳ፣የኬንያ እና የኡጋንዳን ቡና እየጠጡ ስለ ተገፉ ቡድኖች፣ ግለሰቦች እና መብቶች መነጋገር ይቻላል። የዚህ ሀሳብ ጠንሳሽ እና የካፌው ባለቤት ደግሞ ምልዕቲ ብርሃነመስቀል ናት። [...]

መንግስት አመራሮቼ እና አባላቶቼ ላይ የሚያደርሰው እስራት እና ደብዛ ማጥፋት ማጥፋት አማሮኛል ሲል የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ (ኦፌኮ) አመለከተ። ፓርቲው ትናንት ዓርብ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ እየደረሰብኝ ነው ያለው የአመራሮች እና አባላት እስራት እና ደብዛ ማጥፋት የሰላማዊ የፖለቲካ ትግል አቋዋሜን አያናውጥምም ብሏል ። [...]

ባለፈው ሳምንት በአፍሪካ ኅብረት ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ በአካል በመቅረብና ከአፍሪካ ኅብረት የክፍያ ሰነድ ጋር ተመሳስለው የተዘጋጁ የተለያዩ ሐሰተኛ ሰነዶችን በመጠቀም፣ ከአፍሪካ ኅብረት የባንክ ሒሳብ ወደ ሌላ የባንክ ሒሳብ ከስድስት ሚሊዮን ዶላር በላይ ለማዘዋወር ሲሞክሩ በቁጥጥር ስር ውለዋል። [...]

በሶማሊያ የሚገኘው የአፍሪቃ ኅብረት በሶማልያ ያሰማራቸዉን የሰላም አስከባሪ የውጭ አገር ወታደሮች ሁሉ ደረጃ በደረጃ ለማውጣት ተስማምቷል። ህብረቱ የሰላም አስከባሪ ጓዱን ማስወጣት የሚጀምረው ከፊታችን ሰኔ ወር መጨረሻ ጀምሮ እንደሆንም ይጠበቃል። ይሁንና የዉጭ ኃይላቱን የማዉጣቱ ሂደት የሶማሊያን ዜጎች ደህንነት አደጋ ላይ ሊጥስ አይገባም። [...]

የሕዝቡ ምጣኔ ሐብታዊና ማሕበራዊ ፍላጎቶች በመጓደላቸዉ በገዢዉ የANC ፓርቲና በባለስልጣናቱ ላይ ያለዉ ቅሬታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያየለ ነዉ።የምጣኔ ሐብት ተንታኝ ዳንኤል ሲልከ እንደሚሉት ANC ዕዉቁ መሪዉ ኔልሰን ማንዴላ ገቢር ያደረጉትን የሥነ-ምግባር ሥርዓት አለማክበሩ የሐገሪቱን ሕዝብ ክፉኛ አበሳጭቷል። [...]

የአፍሪቃ ሕብረት «የውጭ ምንዛሪ ሒሳቡን ወደ ሌላ ሀገር ሊያዘዋውር ነው» በሚል የተሰራጨው መረጃ «የተሳሳተ» ነው ሲል የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ አስታወቀ። [...]

ዜና