AMHARIC NEWS

  • BBC AMHARIC
  • DW AMHARIC

በምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ውስጥ በሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች ታጣቂዎች ጭፍጨፋ ከፈጸሙ ሁለት ሳምንት ሆነው። በዚህ ጥቃት አብዛኞቹ ሴቶችና ህጻናት የሆኑ በመቶዎቹ የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለዋል። ከእነዚህም መካከል ልጆቻቸውንና የልጅ ልጆቻቸውን ጨምሮ 22 ቤተሰቦቻቸውን በአንድ ጀንበር ያጡት አዛውንት አንዱ ናቸው። አቶ መሐመድ የሱፍ ሁሉ ነገር ጨልሞባቸው 'ከዚህ በኋላ ምን ተስፋ አለኝ' ይላሉ. . . [...]

በመላው ዓለም እጅግ አነጋጋሪ ከሆኑ መካከል ዶ/ር ሩጃ ትጠቀሳለች። ዶ/ር ሩጃ ዋንኮይን በተባለ ክሪፕቶከረንሲዋ ዓለም አቀፍ ዝናን አትርፋ ነበር። ቢልየነሮች በክሪፕቶከረንሲዋ ሃብታቸውን እንዲያፈሱ አሳምናም ነበር። ኋላ ላይ ግን ዶ/ር ሩጃ አጭበርባሪ እንደሆነች ተደረሰባት። [...]

አምስት ጊዜ መንታ ልጆችን የወለዱት ናጄሪያውያን ጥንዶች ቤተሰቦች ደስተኛ ባለመሆናቸው ለመለያየት ተገደው አባት ልጆቹን ብቻውን እያሳደገ ነው። [...]

ተቃዋሚ ሰልፈኞች በምሥራቃዊቷ የሊቢያ ከተማ ቱብሩክ ውስጥ የሚገኘውን የአገሪቱን ፓርላማ ወረው ከፊል ሕንጻውን በእሳት ማቃጠላቸው ተዘገበ። [...]

ባለፈው ወር  ሁለት ብዙም የማይታወቁ ግን በጣም ትልቅ የሆኑ ዲጂታል ገንዘቦች ተንኮታኩተዋል። ይህም በአጠቃላይ በዲጂታል ገበያው ላይ ያለውን አመኔታ አሳጥቷል። ቢትኮይን እና ሌሎች ክሪፕቶከረንሲዎች በእጅጉ ቀንሰዋል። ይህ የሚሆንበት ምክንያት ምንድን ነው? ቢቢሲ የተወሰኑ ነጥቦችን ለይቷል። [...]

የቡሳ ጎኖፋ ኦሮሚያ የምዕራብ ወለጋ ዞን ቅርንጫፍ ኃላፊ ወ/ሮ ነጻነት ዓለማየሁ በአርጆ ጉደቱ ከተማና ቶሌ ቀበሌ ለተጠለሉ ዜጎች ሰብአዊ ድጋፍ መድረሱን ተናገሩ፡፡ ትናንት 7 ተሳቢ መኪና ርዳታ መላኩን ጠቁመዋል፡፡ በቶሌ ቀበሌ ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ድጋፍ እንደ ደረሳቸው የተናገሩ ሲሆን ወደ ሌሎች ስፍራዎች የሸሹ ደግሞ እንዳላገኙ ገልጸዋል፡፡ [...]

የኦፌኮ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ ሙላቱ ገመቹ መንግስት ሰሞኑን ከህወሓት ጋር ድርድር ለማድረግ መዘጋጀቱን ይፋ ባደረገበት መግለጫው ስለሌሎች ታጣቂ ቡድኖች ያለው ነገር አለመኖሩ የድርድሩን ሃቀኝነት ከወዲሁ ጥርጣሪ ውስጥ የሚከት ነው ብለውታል፡፡ [...]

በፖሊቲካል ሳይንስ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን የሰሩትና መመረቂያ ፅሁፋቸውን በዓባይ ወንዝ ላያ ያደረጉት አቶ ተስፋሁን ዓለምነህ በበኩላቸው የሱዳን ትንኮሳ ሁለት ምክንያቶች አሉት አንደኛው የውስጥ ጉዳይ ችግሯን አቅጣጫ ለማስቀየር ሲሆን ሌላው ደግሞ ግብፅን ለማስደሰት ነው ብለዋል፡፡ [...]

የብሪታኒያው ቻታም ሐውስ በትላንትናው ዕለት በኢትዮጵያ የሰላም ግንባታ የሴቶችን ሚና እንዴት ማሳደግ ይቻላል በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ በኢንተርኔት አማካኝነት የተካሔደ ውይይት አዘጋጅቶ ነበር። የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት እና በሌሎች የአገሪቱ አካባቢዎች የሚቀሰቀሱ ግጭቶች በተለይ በሴቶች ላይ ብርቱ ተጽዕኖ ማሳደራቸውን ቻታም ሐውስ ገልጿል። [...]

አወትና ሶርን በዚህ ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ በጀርመን ምክር ቤት መቀመጫ ያገኙ ትውልደ አፍሪቃውያን ናቸው። ከነርሱ በተጨማሪ ከ2013 አንስቶ የቡንደስታግ አባል የሆኑት ትውልደ ሴኔጋላዊው ካራምባ ዲያቢ በዘንድሮው ምርጫ ለሶስተኛ የስራ ዘመን የምክር ቤት መቀመጫ ያሸነፉ አፍሪቃዊ ጀርመናዊ ናቸው። [...]

ዜና