AMHARIC NEWS

  • BBC AMHARIC
  • DW AMHARIC

ሰኞ ሚያዝያ 14/2016 ዓ.ም. የመን ውስጥ በስደት ሲንከራተቱ ቆይተው ወደ አገራቸው ለመመለስ የተነሱ ሰባ ሰባት ኢትዮጵያውያንን አሳፍራ ወደ ጂቡቲ ያቀናችው ጀልባ ወደ ባሕር ዳርቻው ብትቃረብም በሰላም ካሰበችበት አልደረሰችም። በገጠማት የመገልበጥ አደጋ ከ20 በላይ ኢትዮጵያውያን ባሕር ላይ ቀርተዋል። ከአደጋው የተረፈ አንድ ኢትዮጵያዊ አደጋው እንዴት እንደተከሰተ ለቢቢሲ ተናግሯል። [...]

አህጉረ አፍሪካን በፍጥነት በሩጫ በማቋረጥ ክብረ-ወሰን ለመስበር ያለመው ግለሰብ በደኅንነት ስጋት ምክንያት ዕቅዱ ሊከስምበት እንደሆነ ተናግሯል። [...]

በዕድሉ መንገሻ እና አበባ ተስፋዬ በተለያየ ጊዜ ከሱዳን ተነስተው፣ የሊቢያ በርሃን አቆራርጠው፣ የሜድትራኒያንን ባህር ሰንጥቀው ነበር ጣልያን የደረሱት። በዚያ ጉዞ የሰው ልጅ ሊሸከመው የማይችለው ፈተናን አይተዋል። ጭው ባለ በርሃ የሰው ልጆችን የሰውነት ቅሪት እየተመለከቱ፣ እየተደበደቡ፣ እየተራቡ፣ እየተጠሙ እና በህይወታቸው ‘እየቆመሩ’ የተመኟትን ጣልያን ከረገጡ ዓመታትን አስቆጥረዋል። ተስፋ ያደረጓት ጣልያን እንዴት ተቀበለቻቸው? ጣልያን ለኢትዮጵያን ስደተኞች ምን ያህል ምቹ ናት? የቢቢሲ ጋዜጠኞች ጣልያን በሄዱበት ወቅት ታሪካቸውን አጋርተዋል። [...]

ሐሰተኛ ሰነድ በመጠቀም ከስድስት ሚሊዮን ዶላር በላይ ለማውጣት በመሞከር የተጠረጠሩት ቀሲስ በላይ መኮንን፤ ድርጊቱ በተፈጸመበት ቦታ የተገኙት “ሰዎች አታልለዋቸው” እንደሆነ ለፍርድ ቤት መግለጻቸውን ጠበቃቸው አቶ ቱሊ ባይሳ ለቢቢሲ ተናገሩ። [...]

በኬንያ መዲና ናይሮቢ በተከሰተ ከባድ ጎርፍ መንገዶች በውሃ ተጥለቅልቀው የታዩ ሲሆን የሀገሪቱ ባለስልጣን የጎርፉ መጠን “እጅግ በከፋ ደረጃ እየጨመረ ነው” ብለዋል። [...]

አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ፍልስፍና ረዳት ፕሮፈሰር ሲሳይ አሰምሬ የኮሚሽኑን ገለጻ ለመረዳት መቸገራቸውን ይናገራሉ፡፡ “ኮሚሽኑ የታጠቁ አካላት መንግስት ያስረናል ይጮቅነናል በሚል ነው ትጥቅ አንግበው በራሳቸው መንገድ የሚታገሉት [...]

"በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች እየታዩ ያሉ ደም አፋሳሽ ግጭቶች የኮሚሽኑን ሥራ አዳጋች እያደረጉት ይገኛሉ" ሲል ገልጾ የነበረው የምክክር ኮሚሽኑ በመጪው 2016 ዓ. ም አጋማሽ ጥር ዋናውን ጉባኤ ለማካሄድ የሚቻለውን ሁሉ ጥረት እያደረገ መሆኑን ዛሬ አስታውቋል። [...]

ብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን በቀጣይ ዓመት ለሚጀመረው ሀገር አቀፍ ምክክር በየክልሎች እያደረገው ባለው «የተሳታፊ እና የአጀንዳ መነሻ ሀሳቦች ልየታ» ሥራ አብዛኞቹ የፖለቲካ ድርጅቶች አብረውት እየሠሩ መሆኑን አስታወቀ። [...]

በሌላ በኩል ትጥቅ አንስተው ከመንግሥት ጋር ውጊያ ውስጥ የገቡ ኃይላትን ለማነጋገር እየትንቀሳቀሰ መሆኑን ደጋግሞ እየገለፀ ያለውና በብዙዎች ዘንድ እየተጠበቀ ያለው ብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን አቅርቦት የነበረው "አስቸኳይ ሀገራዊ ጥሪ" በጎ ምላሽ እያገኘበት መሆኑን አስታውቋል። [...]

በዛሬው ችሎት ዐቃቤ ሕግ ክስ ማሻሻል ምስክሮችን ለጉዳት የሚዳርግ ነው በሚል ያንን ማድረግ እንደማይችል በጽሑፍ አቤቱታ አቅርቧል። የተከሳሽ ጠበቆችም በበኩላቸው በቃል ክርክር በማድረግ ከሳሽ ዐቃቤ ሕግ የተከሳሾችን ጥያቄ እንዲመልስ ተከራክረዋል። [...]

ዜና