AMHARIC NEWS

  • BBC AMHARIC
  • DW AMHARIC

ሄሊኮፕተሩ የተከሰከሰው በአዘርባጃን ድንበር አቅራቢያ ሲጓዝ እንደነበር የኢራን ባለሥልጣናት ማረጋገጫ ሰጥተዋል። እስካሁን ስለ ሄሊኮፕተሩ አደጋ የምናውቃቸው ነጥቦች ቀጣዮቹ ናቸው። [...]

የዓለም አቀፉ ወንጀል ፍርድ ቤት ዋና ዐቃቤ ሕግ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር እና በጋዛ የሐማሱ መሪ ፈጽመዋቸዋል ባሏቸው የጦር ወንጀሎች የእስር ማዘዣ እንዲወጣባቸው ማመልከቻ አቀረቡ። [...]

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን በመጡ ማግስት በመከላከያ ሚኒስትርነት ተሹመው ለመንፈቅ ያህል ያገለገሉት አይሻ መሃመድ ድጋሚ የአገሪቱ የመከላከያ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ። አይሻ መሃመድ የመከላከያ ሚኒስትር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩትን አብርሃም በላይን (ዶ/ር) እንደሚተኩ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት ዛሬ ግንቦት 12/2016 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል። [...]

የደቡብ አፍሪካ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀድሞው የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ በሚቀጥለው ሳምንት በሚካሄደው ምርጫ ለፓርላማ አባልነት እንዳይወዳደሩ ከለከለ። [...]

በሄሊኮፕተር አደጋ ሕይወታቸው ያለፈው የኢራኑ ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራኢሲ ከኢራን ሃይማኖታዊ መሪ አያቶላ አሊ ኾሜኒ ጋር የጠበቀ ግንኙነት የነበራቸው ጠንካራ ሃይማኖተኛ ነበሩ። ፕሬዚዳንቱ በአውሮፓውያኑ 2021 ወደ ሥልጣን መምጣታቸው በኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ግዛቶች ላይ የወግ አጥባቂዎቹ የበላይነት መስፈንን ያረጋገጠ ነው ተብሏል። [...]

የወላይታ ዞን የሠራተኞቹን ደሞዝ ከቀጣይ ዓመት ተበድሮ ለመክፈል መገደዱን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ ለዶይቼ ቬለ ተናገሩ። የዞኑ የመንግሥት ሠራተኞች ባለፉት ሳምንታት የሦስት ወራት ደሞዛቸው እንዲከፈላቸው አቤት በማለት ይገኛሉ። ከ2009-2012 ባሉት ዓመታት የሠራተኞች ቁጥር ከ23 ሺሕ ወደ 61 ሺሕ ማደጉን አቶ ሳሙኤል ተናግረዋል። [...]

ደሞዝ አልተከፈለንም በሚል ለሁለተኛ ጊዜ በዎላይታ ሶዶ ከተማ ሠልፍ የወጡ የመንግሥት ሠራተኞች አቤቱታቸውን ለማሰማት ወደ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት በማምራት ላይ እንዳሉ በፖሊስ ተበተኑ፡፡ የፀጥታ አባላቱ መንገዱን በፖሊስ ተሽከርካሪዎች በመዝጋት ሠልፈኛው ወደ መጣበት እንዲመለስ ማድረጋቸውን ነው የሠልፉ ተሳታፊዎች የተናገሩት፡ [...]

በተለይም የብልፅግና ጽህፈት ቤት ተወካዩ «እናያለን ታገሱ» የሚል ምላሽ እንደሰጧቸው የጠቀሱት ከተወካዮቹ አንዱ አቶ ብርሃኑ ያዕቆብ«እኛ በረሃብ ላይ እያለን ምን ትዕግስት አለ ፡፡ ምላሻቸው አላረካንም። ርዕሰ መስተዳድሩን አላገኘናቸውም።ጥያቄያችንን እሳቸው ከሄዱበት ሲመለሱ እንደሚያቀርቡልን ተወካያቸው ገልጸውልናል » ብለዋል [...]

አሁን ላይ በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች የደሞዝ ጥያቄ በሚያቀርቡ ሠራተኞች ላይ በፀጥታ አባላት እሥር ፣ ወከባና እንግልት እየተፈጸመ ይገኛል ፡፡ ግንባሩ ይህን ድርጊት የሰብአዊ መብት ጥሰት አካል አድርጎ ይመለከተዋል ፡፡ [...]

ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአፍሪካ ኅብረት አካውንት 6 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ለማጭበርበር ሞክረዋል በሚል በቁጥጥር ሥር ከዋሉ ተጠርጣሪዎች መካከል አራቱ አሁንም በፖሊስ ጣቢያ እንዲቆዩ ፍርድ ቤት አዘዘ። ከተጠርጣሪዎቹ አንዱ የሆኑት የቀሲስ በላይ መኮንን ጠበቆች የዋስትና መብታቸው እንዲከበር ጠይቀዋል። ሁለት ተጠርጣሪዎች ዛሬ ችሎት አልቀረቡም። [...]

ዜና