AMHARIC NEWS

  • BBC AMHARIC
  • DW AMHARIC

ሐሰተኛ ሰነድ በመጠቀም ከስድስት ሚሊዮን ዶላር በላይ ለማውጣት በመሞከር የተጠረጠሩት ቀሲስ በላይ መኮንን፤ ድርጊቱ በተፈጸመበት ቦታ የተገኙት “ሰዎች አታልለዋቸው” እንደሆነ ለፍርድ ቤት መግለጻቸውን ጠበቃቸው አቶ ቱሊ ባይሳ ለቢቢሲ ተናገሩ። [...]

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር “በፀጥታ ችግር” ምክንያት በተቋረጡ እና በቆሙ የመንገዶች ፕሮጀክቶች ላይ 34.95 ቢሊዮን ብር ካሳ በተቋራጮች መጠየቁን አስታወቀ። አስተዳደሩ እስከ 2016 በጀት ዓመት ስድስት ወራት ድረስ “በፀጥታ ችግር” ምክንያት “ሙሉ በሙሉ የኮንትራት ውላቸው የተቋረጠ” 31 የመንገድ ፕሮጀክቶች መኖራቸውንም ይፋ አድርጓል። [...]

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ ህወሓትን ከብልፅግና ፓርቲ ጋር ስለማዋሃድ፣ ስለሰሞኑ ግጭት፣ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ስላለቸው ግንኙነት እና የይገባኛል ጥያቄ ስለሚነሱባቸው አካባቢዎች ለቢቢሲ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። [...]

በአዲስ አበባ ከተማ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ስሙ ጠሮ መስጂድ በተባለ አካባቢ ለቤት ግንባታ የተከመረ ድንጋይ እና አፈር ተንዶ የሰባት ሠዎች ሕይወት አለፈ። [...]

አሜሪካ ውስጥ በድንገት በደረሰ አደጋ ምክንያት ከመንገድ ወጥቶ በእሳት በተያያዘ መኪና ውስጥ የነበረ ግለሰብን ሕይወት ያተረፉ ሁለት ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና ሌሎችም አድናቆት እየተቸራቸው ነው። መኪና ላይ በተገጠመ ካሜራ የተቀረጸው ቪዲዮ እንደሚያሳየው ትውልደ ኢትዮጵያዊያኑ እና ሌሎችም በመንገዱ ላይ ሲያልፉ የነበሩ ሰዎች በእሳት ከተያያዘው መኪና አንድን ግለሰብ ለመታደርግ ያደረጉትን አስደናቂ ጥረት አሳይቷል። [...]

መረጃውን ያጋራው ግለሰብ የቤተሰባቸው አባል የሚገኙበት ዘጠን ሰዎች በምዕራብ አርሲ ዞን አዳባ ወረዳ ወሻ እና ቡቢሳ በተባሉ ቀበሌያት ተገድለው ተጥለው ቢገኙም አንስተው ለመቅበር እንኳ እድሉን መነፈጋቸውን ጠቅሰው ለማን እንንገር በማለት አስተያየታቸውን በሀዘን አጋርተዋል፡፡ [...]

በትውልድ ቀዬያቸው መቂ የተገደሉት የኦነግ የፖለቲካ ኦፊሰር አቶ በቴ ኡርጌሳ ግድያ በኋላ በኦሮሚያ ክልል በህቡዕ ተላልፏል የተባለውን የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ገደብ ጥሪን ተከትሎ አንዳንድ አከባቢዎች ላይ የትራንስፖርት ፍሰት መስተረጓጎል ሲያጋጥም በሌሎች አከባቢዎች ደግሞ እንቅስቃሴው በመደበኛ ሁኔታ ስለመቀጠሉ ተገለፀ፡፡ [...]

አንድ የቤተሰብ አባል በአቶ ቤተ አስከሬን የተለያዩ የሰውነት አካል ላይ በርካታ ያሉት ቦታ ላይ በጥይት ተደብድበው መገደላቸውን የሚያመላክት ብዙ ቁስሎች በአይናቸው መመልከታቸውንም አስረድተዋል። የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የአቶ በቴ ግድያን ተከትሎ ተጠያቂነቱን ወደ መንግስት ለማድረግ የሚደረግ ያለው አሉባልታ ተቀባይነት እንደሌለው አስታውቋል።፡ [...]

በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ባለፉት አስር ቀናት የመንግሥት ጸጥታ አስከባሪዎች እና የታጣቂዎች እንቅስቃሴ መበርታቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ። በተለይ ቶሌ እና አመያ በተባሉ ወረዳዎች ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ይገልጻሉ። [...]

በዚህ ዓመት ከጥር እስከ ሚያዚያ እስራኤል ከጀርመን የገዛችው የጦር መሣሪያ 326.5 ሚሊዮን ዩሮ የወጣበት ነው።ይህም በ2022 ለጦር መሳሪያ ከወጣችው 32 ሚሊዮን ዩሮ በአስር እጅ ይበልጣል። በግዥው ከተካተቱ ውስጥ 20.1 ሚሊዮን ብር የወጣባቸው ፀረ-ታንክ መሣሪያዎች እና የአውቶማቲክና የመለስተኛ አውቶማቲክ ጠመንጃ ጥይቶች ይገኙበታል። [...]

ዜና