AMHARIC NEWS

  • BBC AMHARIC
  • DW AMHARIC

በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነትና በናይሮቢ የትግበራ ሰነድ መሰረት 65 በመቶ የሚሆኑት የትግራይ ኃይሎች ከውጊያ ቀጠናዎች እንዲርቁ መደረጋቸውን ጄኔራል ታደሰ ወረደ አስታወቁ። ሰራዊቱን ከጦርነት ግንባሮች የማራቅ ሂደቱ በከፍተኛ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑንም የትግራይ ኃይሎች ዋና አዛዥ ጄኔራል ታደሰ ወረደ ቅዳሜ ህዳር 24፣ 2015 ዓ.ም ለክልሉ ቴሌቪዥን ጣቢያ ገልጸዋል። [...]

አሜሪካ ኤርትራን ጨምሮ አስራ ሁለት አገራት ከእምነት ነጻነት አንጻር ባላቸው አያያዝ የተነሳ በአሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ናቸው ስትል ፈረጀች። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አንቶኒ ብሊንክን በመሥሪያ ቤታቸው በኩል ባወጡት መግለጫ እንዳመለከቱት፣ ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ነጻነት ደንብን የሚጻረሩ ድርጊቶችን ይፈጽማሉ ያለቻቸውን አገራት በመለየት አሜሪካ ስጋት እንዳላት ገልጸዋል። [...]

የ60 ዓመቱ ባለጸጋ አዳኒ በአሁኑ ወቅትም ከኤሎን መስክ እና ከጄፍ ቤዞስ ቀጥሎ ሦስተኛው የዓለማችን ቱጃር ነው። ወደቦች፣ የኃይል ማመንጫ ኩባንያዎችን ጨምሮ በገበያ ካፒታላይዜሽን ላይ የሚሰሩ ትልልቅ ኩባንያዎች ያሉት አዳኒ በስሩ 23 ሺህ ሠራተኞችን ያስተዳድራል። አንጡራ ሃብቱም 137.6 ቢሊዮን ዶላር ይገመታል። ከሰሞኑ ባለጸጋው የሚዲያዎች መነገጋገሪያ ሆኗል። [...]

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜለንስኪ ምዕራባውያን በሩሲያ ወጪ ንግድ ላይ የጣሉትን የነዳጅ ዋጋ ገደብ “ደካማ” ነው ሲሉ ተቹ። [...]

የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎዛ ከእርሻቸው በተዘረፈው ገንዘብ ጋር ተያይዞ በሙስና ቅሌት ስማቸው ቢነሳም  ከስልጣናቸው እንደማይለቁ ቃለ አቀባያቸው ተናገሩ። [...]

በገፀ ምድር የውሀ ሀብት እምብዛም ባልታደሉት የምስራቅ ሀገሪቱ አካባቢዎች የሀረማያ ሀይቅ ብርቅዬው ሀብት ነው። የውሀው መጠን ቀስ በቀስ ከመቀነስ አልፎ ሙሉ በሙሉ ከገፀ ምድር ድርቆ እስከጠፋበት ጊዜ ድረስ ዘርፈ ብዙ ግልጋሎቶችን ሰጥቷል። [...]

በደቡብ ክልል ሲነሳ የቆየውን በክልል የመደራጀት ጥያቄ ለመመለስ የፌዴሬሽን ም/ቤት በያዝነው ዓመት መግቢያ ላይ አሁን ያለው ክልል በሁለት እንዲከፈል የሚያስችል ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል። [...]

የአፍሪቃ አኅጉር ነጻ የንግድ ቀጣና (AfCFTA) ከ2 ዓመት በፊት ይፋ ሲደረግ በርካታ በአኅጉሪቱ የሚኖሩ ሴት የንግድ ሥራ ፈጠራ ባለሞያዎች ብዙ ተስፋ ሰንቀው ነበር። በዓለማችን ግዙፍ ይሆናል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበት የነበረው የንግድ ቀጠና ታኅሣስ 23 ቀን፣ 2013 ዓ.ም ይፋ ሲደረግ ለ1.2 ቢሊዮን ሰዎች ገበያ ይፈጥራል ተብሎም ነበር። [...]

በርካታ ኢትዮጵያውያን በእንግሊዝኛ ቋንቋ «ሩስያ ቱዴይ» የተባለውን የቴሌቪዥን መርኃ ግብር እንደሚከታተሉም ቤቴልሔም ገልጣለች። ከቤተሰቦቿ ጋር የምታደርገው ንግግርም ብዙውን ጊዜ የሚቋጨው በጭቅጭቅ ነው። [...]

ቻይና በሰብአዊ መብቶች ጉዳይ ከህብረቱ ጋር ንግግር ለመቀጠል መስማማቱን በበጎ ጎኑ እንደሚቀበል የአውሮጳ ህብረት አስታወቀ። የህብረቱ ካውንስል ፕሬዚዳንት ቻርለስ ሚሸል ወደ ቻይና ተጉዘው ከፕሬዚዳንት ዢ ሺንፒንግ ጋር ከተነጋገሩ በኋላ ቻይና ከህብረቱ ጋር በንግድ ፣ በሰላም እና በሰብአዊ መብት ጉዳዮች አብሮ ለመስራት ፍላጎት አሳይታለች። [...]

ዜና