AMHARIC NEWS

  • BBC AMHARIC
  • DW AMHARIC

ከሁለት ቀናት በፊት በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና በሌሎች አገራት አውሎ ንፋስ የቀላቀለው ከባድ ዝናብ የጎርፍ መጥለቅለቅ አስከትሏል። በዩናይትድ አረብ ኤምሬት ታሪክ በ75 ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ መሆኑ የተመዘገበለት ከባድ ዝናብ ተሽከርካሪዎችን ጠርጎ ከመውሰድ በተጨማሪ የተለያዩ ንብረቶች ላይ ጉዳቶች አድርሷል። ለመሆኑ በነዚህ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በምን ሁኔታ ላይ ይገኛሉ? [...]

ኢራን ከግብፅ ቀጥላ ለእስራኤል እውቅና በመስጠት ሁለተኛዋ እስላመዊ አገር ነበረች። ነገር ግን ከኢራን እስላማዊ አብዮት በኋላ ይህ ግንኙነት ተበላሽቶ ከአምስት አስርታት በላይ በጠላትነት እየተያዩ ቆይተዋል። ለመሆኑ የሁለቱ አገራት ግንኙነት ወደ ደመኛ ጠላትነት ለምን ተሸጋገረ? [...]

ጀርመን ለዩክሬን የምትሰጠውን ወታደራዊ ድጋፍ ለማደናቀፍ ሲያሴሩ ነበር የተባሉ በስለላ የተጠረጠሩ ሁለት ግለሰቦች ደቡባዊ ግዛቷ ባቫሪያ ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋሉ። [...]

ባለፈው ሰኞ በአውስትራሊያ ሲድኒ ከተማ በቀጥታ በሚተላለፍ ሰብከት ላይ ሳሉ በስለት ጥቃት የደረሰባቸው አቡነ ማር ማሪ ኢማኑኤል በፍጥነት እያገገሙ እንደሆነ ገልጸው፣ ጥቃቱን እንዳደረሰ ለተጠረጠረው ግለሰብም ይቅርታ እንዳደረጉ ተናግረዋል። [...]

ባለፈው ዓመት የተቀሰቀሰው የሱዳን ጦርነት ክርስቲያኖችን አጣብቂኝ ውስጥ ከቷቸዋል። በጦርነቱ መጀመሪያ አካባቢ ክርስቲያኖች በተለየ መልኩ ተጠቅተዋል የሚሉ መረጃዎች ሲወጡ ነበር። አብያተ ክርስቲያናት ተዘርፈዋል፤ አንዳንዶቹም በከባድ መሣሪያ ጥቃት ደርሶባቸዋል። ከአንድ ዓመት በኋላ ብዙዎቹ ወደ ግብፅ ሲሰደዱ፣ ቀሪዎቹም ተጠልለው ከሚገኙበት ፖርት ሱዳን ለመሰደድ አማራጮችን እየፈለጉ ነው። [...]

የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግሥት «ህወሓትና ግብረ አበሮቹ» ያላቸው አካላት ሁለቱ ወገኖች የይገባኛል ጥያቄ ከሚያነሱባቸውና ሰሞኑን በኃይል ከያዟቸው አካባቢዎች በአስቸኳይ እንዲወጡ አሳሰበ። የአማራ ክልላዊ መንግሥት በመግለጫው የፕሪቶሪያው ስምምነት እንዲተገበርም ጠይቋል። [...]

ከትግራይ ክልል የተነሱ ታጣቂዎች በራያ አላማጣ ወረዳ አንዳንድ ቀበሌዎች ሰሞኑን ጥቃት ማድረሳቸውን የአካባቢው ነዋሪዎችና አስተዳደሩ ተናገሩ። በግጭቱ የሰዎች ሕይወት መጥፋቱን ንብረት መውደሙንም ናዋሪዎቹና የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶቼ ቬሌ ገልጸዋል። [...]

የጦርነቱ ጠባሳ ከአንድ ዓመት ከመንፈቅ ግድም በኋላም በጉልኅ ይታያል ። ባለፉት ሳምንታት በትግራይ እና አማራ ክልሎች ውስጥ በሚገኙ ታጣቂዎች መካከል ለአጭር ጊዜያት የቆዩ ግጭቶች ከአንዴም ሁለት ጊዜ መከሰታቸው ነዋሪዎችን እጅግ አስግቷል ። [...]

ትግራይ የሚገኙ የጦርነቱ ተፈናቃዮች፥ መንግስት ወደቀዬአቸው እንዲመልሳቸው ጥሪ አቀረቡ። የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር በበኩሉ ከጦርነቱ በኋላ በአካባቢዎቹ የተቋቋሙ አስተዳደሮች ባለመፍረሳቸው እና ታጣቂዎች ባለመውጣታቸው ምክንያት ተፈናቃዮች የመመለስ ስራ አስቸጋሪ አድርጎታል ይላል። [...]

ባለሙያዎች እንደሚሉት በተንቀሳቃሽ ስልኮች፣በታብሌት፣በቴሌቪዝን እና በሌሎች ዲጅታል መሳሪያዎች ላይ ረዘም ያለ ጊዜ የሚያሳልፉ ልጆች ለጭንቀት እና ለመረበሽ፣ ለትኩረት ማጣት፣ ለንግግር እና ለቋንቋ መዘግየት እንዲሁም ለግንዛቤ እድገት ውሱንነት ይዳረጋሉ። የሰዎችን ስሜት የመረዳት እና የመግባባት ችሎታቸውንም ይቀንሳል። [...]

ዜና