AMHARIC NEWS

  • BBC AMHARIC
  • DW AMHARIC

ሐሰተኛ ሰነድ በመጠቀም ከስድስት ሚሊዮን ዶላር በላይ ለማውጣት በመሞከር የተጠረጠሩት ቀሲስ በላይ መኮንን፤ ድርጊቱ በተፈጸመበት ቦታ የተገኙት “ሰዎች አታልለዋቸው” እንደሆነ ለፍርድ ቤት መግለጻቸውን ጠበቃቸው አቶ ቱሊ ባይሳ ለቢቢሲ ተናገሩ። [...]

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር “በፀጥታ ችግር” ምክንያት በተቋረጡ እና በቆሙ የመንገዶች ፕሮጀክቶች ላይ 34.95 ቢሊዮን ብር ካሳ በተቋራጮች መጠየቁን አስታወቀ። አስተዳደሩ እስከ 2016 በጀት ዓመት ስድስት ወራት ድረስ “በፀጥታ ችግር” ምክንያት “ሙሉ በሙሉ የኮንትራት ውላቸው የተቋረጠ” 31 የመንገድ ፕሮጀክቶች መኖራቸውንም ይፋ አድርጓል። [...]

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ ህወሓትን ከብልፅግና ፓርቲ ጋር ስለማዋሃድ፣ ስለሰሞኑ ግጭት፣ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ስላለቸው ግንኙነት እና የይገባኛል ጥያቄ ስለሚነሱባቸው አካባቢዎች ለቢቢሲ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። [...]

በአዲስ አበባ ከተማ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ስሙ ጠሮ መስጂድ በተባለ አካባቢ ለቤት ግንባታ የተከመረ ድንጋይ እና አፈር ተንዶ የሰባት ሠዎች ሕይወት አለፈ። [...]

አሜሪካ ውስጥ በድንገት በደረሰ አደጋ ምክንያት ከመንገድ ወጥቶ በእሳት በተያያዘ መኪና ውስጥ የነበረ ግለሰብን ሕይወት ያተረፉ ሁለት ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና ሌሎችም አድናቆት እየተቸራቸው ነው። መኪና ላይ በተገጠመ ካሜራ የተቀረጸው ቪዲዮ እንደሚያሳየው ትውልደ ኢትዮጵያዊያኑ እና ሌሎችም በመንገዱ ላይ ሲያልፉ የነበሩ ሰዎች በእሳት ከተያያዘው መኪና አንድን ግለሰብ ለመታደርግ ያደረጉትን አስደናቂ ጥረት አሳይቷል። [...]

በአማራና ትግራይ የይገባኛል ጥያቄ በሚነሳባቸው አካባቢዎች በተከሰተ ግጭት ከ50 ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ እርዳታ ማስተባበሪያ ያለፈው ሰኞ አስታውቋል። እንደ ድርጅቱ በሺህዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሲሆን፤ በተለይ ሴቶችና ህጻናት የሚገኙበት ሁኔታም አሳሳቢ ነው። [...]

በትግራይና አማራ አዋሳኝ አካባቢዎች የተከሰቱ ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ ብቻ መፈታት እንዳለባቸው ምሁራን አመለከቱ። [...]

“ከትግራይ ክልል ተሻግረው የመጡ” ያሏቸው ታጣቂዎች ጥቃት እንዳደረሱባቸው የራያ አላማጣ ወረዳ ባለስልጣናትና ነዋሪዎች ለዶይቼ ቬሌ ተናገሩ። ጉዳዩን አስመልክቶን ከትግራይ ክልል የመንግስት የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃአስተያየት ለማካተት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡ የፕሪቶሪያው ስምምነት በህገመንግስቱ መሰረት እንደሚፈታ ዉሉ ያትታል፡፡ [...]

ከአላማጣ ከተማ ተፈናቅለው በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ ጃራ የመጠለያ ጣቢያ ከአንድ ዓመት በላይ ይኖሩ የነበሩ የአላማጣ ከተማ ተፈናቃዮች በመንግስት ድጋፍ ትናንት ወደ ቀያቸው መመለሳቸውን የአካባቢው አስተዳደርና ተፈናቃዮች ተናገሩ፣ በመጠለያ ጣቢያው ከአላማጣ፣ ባላ፣ ኮረምና ኦፍላ የተፈናቀሉ ከ 30 ሺህ በላይ ሰዎች ይኖሩበት ነበር ተብሏል፡፡ [...]

ከብልፅግና ጋር የሚያገናኘው የጋራ አጀንዳው የፕሪቶርያው ውል መሆኑን የገለጸው ህወሓት ውሉ በሙሉ እንዲተገበር አጋዥ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ብልፅግና ፓርቲና ህወሓት በመቐለና አዲስአበባ መወያየታቸውን አስታውቋል። ከዚህ ውጭ ህወሓትና ብልፅግና ፓርቲ በመገናኛ ብዙሐን እንደተባለው የጀመሩት ወደ ውህደት የሚመራ ውይይት የለም ሲል አስተባብሏል። [...]

ዜና