AMHARIC NEWS

  • BBC AMHARIC
  • DW AMHARIC

በገዢው ብልፅግና ፓርቲ በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ስር የሚንቀሳቀሱ እና ‘የሚዲያ ሠራዊት’ የሚል መጠሪያ ያላቸው የፓርቲው አባላት፤ መንግሥትን በሚተቹ እና በሚቃወሙ ግለሰቦች ላይ በፌስቡክ በተደረጉ የሐሰተኛ መረጃ እና በተቀናጁ ዘመቻዎች ላይ እንደተሳተፉ ቢቢሲ ያደረገው ምርመራ አረጋገጠ። [...]

እስራኤል ባለፈው ቅዳሜ ኢራን ለፈጸመችባት የድሮን እና የሚሳኤል ጥቃት ዛሬ ማለዳ ላይ የአጸፋ ጥቃት መፈጸሟን የኢራን መገናኛ ብዙኃን እና የአሜሪካ ባለሥልጣናት አስታወቁ። [...]

ከአስር ዓመት በፊት በቦኮሃራም ታጣቂዎች ታግተው ከነበሩ ሴቶች መካከል አንዷ የሦስት ልጆች እናት ሆና በናይጄሪያ መንግሥት ወታደሮች ነጻ ወጣች። [...]

በኢትዮጵያ ከሚገኙ የሁለተኛ እና ሶስተኛ ክፍል ተማሪች 56 በመቶዎቹ ምንም ዓይነት ቃል ማንበብ እንደማይችሉ ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ባደረገው ጥናት አመልክቷል። አገልግሎቱ በጥናቱ ተሳተፊ ካደረጋቸው የሁለተኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል ቢያንስ አንድ ቃል ማንበብ የሚችሉ 37 በመቶ የሚሆኑት ብቻ እንደሆኑ በአገልግሎቱ የትምህርት ምዘናና ምርምር መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤፋ ጉርሙ (ዶ/ር) ለቢቢሲ ገልጸዋል። የተቀሩት 63 በመቶዎቹ አንድም ቃል ማንብብ የማይችሉ (Zero renderers) ናቸው። [...]

የኬንያ ጦር አዛዥ ጄኔራል ፍራንሲስ ኦሞንዲ ኦጎላ በምዕራብ የአገሪቱ ክፍል ይበሩበት የነበረው ወታደራዊ ሄሊኮፕተር ተከስክሶ ሕይወታቸው ማለፉን ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ አስታወቁ። [...]

የወልቃይት፣ ጠገዴ ጠለምትና ራያ ጉዳይ በፖለቲካዊ ውሳኔ እንዲፈታ በአሜሪካ የሚገኙ 8 ኢትዮጵያ ሲቪክ ድርጅቶች ጥሪ አቀረቡ። [...]

የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግሥት «ህወሓትና ግብረ አበሮቹ» ያላቸው አካላት ሁለቱ ወገኖች የይገባኛል ጥያቄ ከሚያነሱባቸውና ሰሞኑን በኃይል ከያዟቸው አካባቢዎች በአስቸኳይ እንዲወጡ አሳሰበ። የአማራ ክልላዊ መንግሥት በመግለጫው የፕሪቶሪያው ስምምነት እንዲተገበርም ጠይቋል። [...]

ከትግራይ ክልል የተነሱ ታጣቂዎች በራያ አላማጣ ወረዳ አንዳንድ ቀበሌዎች ሰሞኑን ጥቃት ማድረሳቸውን የአካባቢው ነዋሪዎችና አስተዳደሩ ተናገሩ። በግጭቱ የሰዎች ሕይወት መጥፋቱን ንብረት መውደሙንም ናዋሪዎቹና የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶቼ ቬሌ ገልጸዋል። [...]

የጦርነቱ ጠባሳ ከአንድ ዓመት ከመንፈቅ ግድም በኋላም በጉልኅ ይታያል ። ባለፉት ሳምንታት በትግራይ እና አማራ ክልሎች ውስጥ በሚገኙ ታጣቂዎች መካከል ለአጭር ጊዜያት የቆዩ ግጭቶች ከአንዴም ሁለት ጊዜ መከሰታቸው ነዋሪዎችን እጅግ አስግቷል ። [...]

በተለይም ከቅርብ ቀናት ወዲህ በትግራይ እና አማራ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ግጭቶች እያገረሹ ይገኛሉ። በዚህም ሞትና መፈናቀል ተከስቷል። የሁለቱ ክልል አስተዳደሮችም እርስ በራሳቸው እየተወነጃጀሉ ይገኛሉ። [...]

ዜና