AMHARIC NEWS

  • BBC AMHARIC
  • DW AMHARIC

በአገሪቱ ውስጥ ያሉ አለመግባባቶች እና ችግሮችን በሕዝባዊ ውይይት ለመለየት እና መፍትሔ ለማፈላለግ የተቋቋመው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሁለት ዓመት ሆነው። ነገር ግን በአገሪቱ ያሉ ችግሮች እየተወሳሰቡ በመሄድ ላይ ናቸው። በዚህም በኮሚሽኑ ሥራ እና ሚና ላይ ጥያቄ የሚያነሱ ወገኖች አሉ። ከሚነሱ ነገሮች መካከል ቢቢሲ የተወሰኑትን አንስቶ ኮሚሽነሩን ፕሮፌሰር መሥፍን አርአያን ጠይቋል። [...]

የአማራ እና ትግራይ ክልሎች ይገባናል በሚሉት የራያ አላማጣ ወረዳ ሰኞ ዕለት በተከሰተ ግጭት የአራት ሚሊሻዎች ሕይወት መጥፋቱን የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ተናገሩ። መጋቢት 16/2016 ዓ.ም. በተፈጠረው ግጭት ከሞቱት በተጨማሪ ሌሎች አስራ ሁለት ሰዎች ደግሞ ቀላል እና ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው አስተዳዳሪው አቶ ሞላ ደርበው ለቢቢሲ ገልጸዋል። [...]

ታጋቾችን ለማስፈታት የሚካሄደው ንግግር አለመሳካቱን ተከትሎ ለተቃውሞ ወደ ቴል አቪቭ አደባባዮች ወጥተው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል የታጋች ቤተሰቦች እንደሚገኙበት ታውቋል። [...]

በፈረንሳይ ትምህርት ቤት ውስጥ አንዲት ሙስሊም ታዳጊ “መምህሬ የጸጉር መሸፈኛ ጨርቄን እንዳወልቅ ጥቃት አድርሶብኛል” ስትል ያቀረበችው ውንጀል ሀሰተኛ ነው ያለው መንግሥት ታዳጊዋን እንደሚከስ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ተናገሩ። [...]

የጊኒ ቢሳው የቀድሞ ፕሬዚዳንት ልጅ በአገሩ መፈንቅለ መንግሥት ማካሄድ ይችል ዘንድ አለም አቀፍ የአደንዛዥ ዕጽ ዝውውርን ይመራ ነበር ተባለ። [...]

አፍሮ ባሮ ሜትር የተባለዉ ተቋም ይፋ ባደረገዉ ጥናቱ መሠረት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እየተባባሰና የድህነት ደረጃም እየጨመረ ነዉ።በአፍሪካ ተሞክሮዎች እና ግምገማዎች በ39 ሀገሮች ላይ ገለልተኛ ሆኖ ይሰራል የሚባለው ይህ ተቋም በኢኮኖሚ፣ በግል ኑሮ ሁኔታ እና በድህነት ልኬት ላይ ያደረገው ጥናት እንዳመለከተዉ ኢትዮጵያ መልካም ሁኔታ ውስጥ አይደለችም [...]

ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ቀደም ሲል ወደ አገሪቱ ይጎርፍ የነበረው የውጭ ምንዛሪ ፣በጦርነቱ ሳቢያ ተቋርጦአል፡፡ በውጭ አገር የሚኖሩትም የአገሪቱ ልጆች ዶላሩንና ዩሮውን ወደ ኢትዮጵያ ማስተላለፉን „አኩረፈው“ እነሱም ቧንቧውን ዘግተዋል፡፡ኑሮ ተወዶአል፡፡ ጥራጥሬዎች በአንድ ምሽት ብቻ ጨምረው ዋጋቸው አይቀመስም፡፡ [...]

አፍሪቃ ውስጥ በርካታ የክርስትና እና እስልምና ተከታዮች ይገኛሉ። ጸሎት አይለያቸውም፣ ሃይማኖታቸውንም አክብረው ይይዛሉ። በሌላ በኩል ደግሞ በዚች አህጉር ላይ ሙስና እጅጉን ተስፋፍቷል። ሃይማኖት፣ ድህነት እና ሙስና የሚያገናኛቸው ነገር አለ? የኢትዮጵያ ወጣቶችስ ምን ይላሉ? [...]

ባለፉት ሁለት ወራት 33,336 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ አገራቸው ተመልሰዋል። ባህርና በረሐ አቋርጠው፤ ከሞት ግብግብ ገጥመው ሳዑዲ አረቢያ ደርሰው ከተመለሱ መካከል ህልማቸው የጨነገፈ ይገኙበታል።ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸው ድህነትን መርታት፣ ቤተሰቦቻቸውን ማገዝ የሚሹ ነበሩ። በዚህ ጥንቅር መንገዱን፣ ሥራውን፣ እስርና ስቃዩን ይተርኩታል። [...]

በአመት 130ሺ ማለት በቀን ከ 350 በላይ የአእምሮ ህመምተኞች ወደ ሆስፒታሉ ይመጣሉ። ሀኪሞቹም በሰአት በአማካይ 44 ህመምተኞችን ያክማሉ ማለት ነዉ።80% የሚሆኑት ወደ ሆስፒታሉ የሚመጡት ከባድ የአእምሮ ህክምና እና ክትትል የሚይስፈልጋቸው ናቸው [...]

ዜና